- 2

Amharic Language, Literature And Folklore Project Topics

Get the Complete Project Materials Now! »

የዚህ ጥናት ዓቢይ ዓላማ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ ማጥናት ነዉ፡፡ ጥናቱ የተካሄደው በአዲስ አበባ ከተማ ውሰጥ ከሚገኙ የመንግስት ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በናሙናነት በተመረጡት ሦስት ትምህርት ቤቶች የዘጠነኛ ከፍል ተማሪዎች ላይ ነው፡፡ ሁሉንም የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎቸ በጥናቱ ውስጥ ማካተትም ከአቅም በላይ ስለሆነ የተወሰኑ ተማሪዎች በናሙናነት ተመርጠው ጥናቱ ተካሂዳል፡፡rnለጥናቱ ያገለገሉት የመረጃ ማሰባሰቢያ መሣሪያዎእን ለመምህራን የተሠራጨ የጹሑፍ መጠይቅ፤ የክፍል ውስጥ የንባብ ትምህርት ምልከታ እና አንብቦ የመረዳት ፈተና ናቸው፡፡ መምህራንን የጹሑፍ መጠይቅ በማስምላት፤ በክፍል ውስጥ በሚሰጠው የንባብ ትምህርት ላይ ምልከታ በማካሄድ፤ ለተጠኝ ተማሪዎቹ አንብቦ የመረዳት ፈተና በመፈተን መረጃዎችን ተሰባስበዋል፡፡ የተሰበሰቡት መረጃዎችም ተተንትነዋል፡፡rnበጥናቱ የተገኘው ውጤት ጥናቲ የሚመለከታችው ተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታቸው ዝቅተኛ እንደሆነ ያሳያል፡፡ለተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታ ዝቅተኛ መሆን ከሚጠቀሱት ውስጥ ዋንኞቹ የትምህርቲ አሠጣጥና የመማሪያ መጽሐፍ በዋነኝነት ይጠቀሳሉ፡፡ በመጠይቅ በተሰበሰቡት መረጃዎች መሠረት ንባብን ከማሰተማሩና ከመማሪያ መጽሐፍ አኳያ ችግሮች አሉ፡፡ በክፍል ውስጥ የሚሰጠው የንባብ ትምህርት ተማሪዎችን እንደማያሳትፍ፤ አብዛኞቹ ተግባራት በመምህሩ እንደሚከናወኑ፤ ተማሪዎቹ በቂ ልምምድ እንደማያደርጉ በምልከታ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

Get Full Work

Report copyright infringement or plagiarism

Be the First to Share On Social



1GB data
1GB data

RELATED TOPICS

1GB data
1GB data
-   2

300