( ) ()

Amharic Language, Literature And Folklore Project Topics

Get the Complete Project Materials Now! »

ይህ ጥናታዊ ጽሁፍ የዳንግላው ሼህ ሁሴን አለሙን የመውሊድ ክብረ በአል እና በመውሊዱ ላይrnየሚከወኑ ቃላዊ ግጥሞች ክዋኔ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡ በጥናቱ የተነሱ ሁለት ዋና የምርምርrnጥያቄዎች የሐጅ ሁሴይን (የሼህ ዳንግላ) የመውሊድ ስርዓተ ክዋኔ ምን ይመስላል? እና በመውሊድrnስርዓተ ክዋኔው ላይ የሚቀርቡት ቃላዊ ግጥሞች ክዋኔ ከሐይማኖታዊ ገጽታቸው ባሻገር ምን አይነትrnፎክሎራዊ ገጽታ አላቸው የሚሉ ናቸው፡፡ ከቤተ መጻህፍት በተገኙ ስራዎች እና የጥናት ወረቀቶችrnላይ ንባብ የተካሄደ ሲሆን ምልከታ፣ ቃለመጠይቅ እና የቡድን ውይይትን በመጠቀም ከመስክ መረጃrnተሰብስቧል፡፡rnበዚህም መሰረት የሐጅ ሁሴን (የሼህ ዳንግላ) የመውሊድ ስርዓተ ክዋኔ ምን ይመስላል? ለሚለውrnመሰረታዊ ጥያቄ የመውሊድ በአሉ የየራሳቸው ዓላማ ያላቸው ሁነቶች ድምር ውጤት መሆኑንrnለማወቅ ተችሏል፡፡ በመውሊድ በዓሉ የአከባበር ስርዓት ላይ በዋናነት የተስተዋሉትን የክዋኔ ሁነቶችrnዚያራ፣ ዱኣ፣ ምርቃት እና መንዙማ ናቸው፡፡ የነዚህ ሁነቶች አጠቃላይ መጠሪያ “ሐድራ” ሲሆንrn“ዱኣ” የሚለውን ምትክ እንደሆነ በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሁነቶቹ አንዱ ከአንዱrnጋር ጥብቅ የሆነ ቁርኝት ያላቸው እንደመሆናቸው ተሳታፊዎቹም ይህንን አውቀው ይፈጽሟቸዋል፡፡rnበዚህ ጥናት በሁለተኛነት የተነሳው ጉዳይ በመውሊድ ስርዓተ ክዋኔው ላይ የሚቀርቡት ቃላዊ ግጥሞችrnክዋኔ ከሐይማኖታዊ ገጽታቸው ባሻገር ምን አይነት ፎክሎራዊ ገጽታ አላቸው? ለሚለው መሰረታዊrnጥያቄ የመንዙማ ግጥሞች በተከወኑበት የክዋኔ ሒደት (በሐድራው ላይ በሚቀርቡበት መንገድ) አንጻርrnበሁለት መንገድ (በድቤና በእንጉርጉሮ) እንደሚባሉ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በዚህም መሰረት በድቤrnየሚቀርቡት ክዋኔያቸው አሳታፊ ሲሆን በእንጉርጉሮ በሚቀርቡት ላይ ግን ታዳሚዎቹ ከዋኙንrnማድመጥ ሚናቸው መሆኑን ለማዎቅ ተችሏል፡፡ በተጨማሪም ከመንዙማዎቹ ክዋኔ ጋር በተገናኘrnየቃላዊ ግጥሞቹን ክዋኔ ለማጀብ የሚያገለግሉ ቁሳዊ ባህሎች (ድቤ፣ የድቤ መምቻና ከበል) በክዋኔውrnሂደት ካላቸው ሚና አንጻር፤ ለመንዙማ ግጥሞቹ ክዋኔ የሚሰጡት ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ለማዎቅrnተችሏል፡፡rnበአጠቃላይ እነዚህ የመንዙማ ግጥሞች በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ከማኅበራዊ፥ ታሪካዊ፥ ፖለቲካዊናrnሃይማኖታዊ ጠቀሜታ በተጨማሪ ያላቸው ባህላዊ፣ ፎክሎራዊና ኪነ ጥበባዊ ዋጋ እጅግ ከፍተኛrnበመሆኑ ወደፊት ሰፋ ባለ ጥናት ቢጠኑ መልካም ነው የሚል ጥቆማ በመስጠት ጥናቱ ተጠናቋል፡፡

Get Full Work

Report copyright infringement or plagiarism

Be the First to Share On Social



1GB data
1GB data

RELATED TOPICS

1GB data
1GB data
( )      ()

241