( 7

Amharic Language, Literature And Folklore Project Topics

Get the Complete Project Materials Now! »

የጥናቱ ዋና ዓላማ የአፍ መፍቻ ቋንቋን በትምህርት መስጫነት በመጠቀም ረገድ እየታዩ ያሉ አመለካከቶችንና እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን ማጥናት ነው፡፡ ዓላማውን ለማሳካትም የጥናቱ ንድፍ ውህድ ዘዴን የተከተለ ሲሆን ከውህድ ጥናት ንድፍ ንኡስ ክፍሎችም ባለትይዩ አቻ ውህድ ዘዴ (convergent parallel mixed method) ተግባራዊ የተደረገበት ነው፡፡ ለጥናቱ አስተማማኝ መረጃዎችን ለማግኘትም ቅንጅታዊ የምርምር ዘዴ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ የጥናቱ ቦታም የደቡብ ኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልልን ሲሆን፣ በዚህ ክልል ውስጥ “medium MT exit model”ን (ከአንደኛ እስከ አራተኛ ክፍል) ከሚጠቀሙ ዞኖች መካከል ስልጤን፣ ወላይታን፣ ከምባታንና ሀድያን በእጣ ንሞና በመምረጥ በጽሁፍና በቃል መጠይቅ መረጃ ተሰብስቧል፡፡ በእነዚህ ዞኖች ውስጥም በ18 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ በስምንት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ በሁለት የመምህራን ኮሌጆች፣ በስምንት የገጠርና የከተማ ቀበሌዎች፣ በ12 የዞንና የወረዳ ትምህርት መምሪያዎች ከወላጆች፣ ከመምህራን፣ ከተማሪዎች፣ ከትምህርት ባለሞያዎችና ሀላፊዎች መረጃ ተሰብስቧል፡፡rnየተገኙ መረጃዎችም በየንዑስርዕሰ ጉዳዮች ስር ተደራጅተው በገላጭ የትንተና ስልት ተተንትነዋል፡፡ ትንተናውን ለማካሄድም የማህበራዊ ሳይንስ ጥናት መረጃዎችን ለመተንትን የተዘጋጀው የኮምፒተር ፕሮግራም SPSS /Statistical Package for the Social Science/ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ የጥናቱ ግኝቶች እንዳመለከቱትም አብዛኞቹ የጥናቱ ተተኳሪዎች የአንደኛ ደረጃ ትምህርት በአፍ መፍቻ ቋንቋ በመሰጠቱ ደስተኞች እንደሆኑና እንደሚደግፉ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ከአንደኛ እስከ አራተኛ ክፍል) ባለፈ ግን ለትምህርት መስጫነት ከአፍ መፍቻ ቋንቋ ይልቅ እንግሊዝኛን እንደሚመርጡ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የአመለካከቶቹ መንስኤዎችም ባብዛኛው ኢኮኖሚያዊ፣ ስነትምህርታዊና ስነልቦናዊ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ሌላው የተግዳሮት ጉዳይ ሲሆን፣ በአፍ መፍቻ ቋንቋ በማስተማር ሂደት ላይ አብይ ተግዳሮት ሆኖ በዚህ ጥናት የተገኘው ስነትምህርታዊ ተግዳሮት ነው፡፡ የዚህም መንስኤው ባብዛኛው የፖለቲካ ቁርጠኝነት አለመኖር እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በመጨረሻም ከጥናቱ ግኝቶች በመነሳት አስተያየቶች ቀርበዋል፡፡ የወደፊት የምርምር አቅጣጫዎችም ተጠቁመዋል፡፡

Get Full Work

Report copyright infringement or plagiarism

Be the First to Share On Social



1GB data
1GB data

RELATED TOPICS

1GB data
1GB data
(              7

241